በዚች ሀገር የፖለቲካ ፓርቲ ማደራጀት ፍጹም አይቻልም ተብሏል
ኢስዋትኒ ያለ ምንም ፓርቲ ምርጫ ማድረጓ ተገለጸ።
የቀድሞዋ ስዋዚላንድ የአሁኗ ኢስዋትኒ የህግ አውጪ ምክር ቤት ባሳለፍነው አርብ አድርጋለች።
አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የህዝብ ብዛት ያላት ይህች ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር በአፍሪካ ብቸኛዋ ንጉሳዊ አስተዳድር ያላትም ሀገር ነች።
በኢስዋትኒ የተቃዋሚ ፓርቲ ማደራጀት የማይቻል ሲሆን ይህ ቢሆንም ግን ምርጫ ማካሄዷን ኤፒ ዘግቧል።
- የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ መሪዎች ስዕል በፓሪስ ለእይታ ቀረበ
- የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ መሪዎች ስዕል በፓሪስ ለእይታ ቀረበ
ሀገሪቱ በንጉሳዊ አስተዳድር ስትመራ 55 ዓመት የሆናት ሲሆን ምስዋቲ ሶስተኛ ደግሞ የሀገሪቱ ንጉስ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካ እና ሞዛምቢክ የምትዋሰነው ኢስዋትኒ ከፈረንጆቹ 1973 ጀምሮ ፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋምን በይፋ የሚከለክል ህግ አላት።
በዘንድሮው ምርጫ 500 ሺህ ህዝብ ለመራጭነት ተመዝግበዋል የተባለ ሲሆን አፍሪካ ህብረት እና የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ጥምረት ወይም ሳድክ የምርጫ ታዛቢዎችን እንዳላከ ተገልጿል።
በዓለም ካሉ ድሀ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢስዋትኒ በሙስና፣ በመሰረተ ልማት እጥረት እና በሌሎች ችግሮች የከፋ ችግሮችም እንዳሉባት የዓለም ባንክ አስታውቋል።