የሀገሪቱ ጁንታ ዋና ትኩረቱ የደህንነት ጉዳይ መሆኑን ተናግሯል
የቡርኪናፋሶ ጁንታ መሪ ኢብራሂም ቴራሬ ሀገሪቱ ተረጋግታ ለሁሉም ሰው እንዲመርጥ የሚያስችል ሰላም ከለሌ ምርጫ እንደማይደረግ አስታውቀዋል።
ባለፈው ዓመት መንግስት ገልብጦ ስልጣን የጨበጠው ወታደራዊ መንግስት፤ ህዝባዊ አገዛዝን ለመመለስ በ2024 ምርጫ አደርጋለሁ ብሎ ነበር።
ኢብራሂም ቴራሬ የመፈንቅለ መንግስቱን አንደኛ ዓመት አስመልክተው በደጋፊዎቻቸው ፊት ባደረጉት ንግግር፤ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ሲፈቅድ ምርጫው እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ቴራሬ ባለፈው ዓመት በጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 30 ፕሬዝዳንት ሮክ ካቦሬን ከስልጣን ካወረደው የሌላ የመፈንቅለ መንግስት መሪ ስልጣኑን ተቆጣጥረዋል።
መንግስት ግልበጣዎቹ ከአልቃይዳ እና እስላማዊ መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂ ቡድኖች ባስከተሉት የጸጥታ ችግር ምክንያት የተቀጣጠሉ ናቸው።
የመስከረሙ መፈንቅለ መንግስት በሀገሪቱ የደህንነት ሁኔታ ተስፋ በቆረጡ ዜጎች በደስታ ተቀብለውታል።
ሆኖም ምዕራባዊያን ተጽዕኗቸው እየቀነሰ ባለበት በአፍሪካ ሳህል ክልል የዲሞክራሲ ስጋት ነው ሲሉ አውግዘውታል።
ጁንታው መንግስት ቀደም ሲል ሀምሌ 2024 የሲቪል አገዛዝን ለመመለስ ምርጫ ለማካሄድ ወስኖ ነበር።
ነገር ግን ቴራሬ ዋና ትኩረታቸው የደህንነት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
ጊዜያዊ መሪው በመንግስት ቴሌቪዥን ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሁሉም ሰው መምረጥ እስኪችል ድረስ ምርጫ እንደማይደረግ ገልጸዋል።