የኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ደንበኞቼ 72 ሚሊዮን እንደደረሱለት ገልጿል
ኢትዮ ቴሌኮም በታሪክ ትልቁን ገቢ በዚህ ዓመት ማግኘቱን አስታወቀ።
የኢትዮ ቴሌሎም ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
ስራ አስፈጻሚዋ በመግለጫቸው እንዳሉት ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 75 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል።
ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ውስጥም 44 በመቶው ከድምጽ ጥቅል ሲገኝ 23 በመቶው ከኢንተርኔት አገልግሎት መገኘቱን ስራ አስፈጻሚዋ አክለዋል።
- የፈረንሳይና የአረብ ኢምሬት ኩባንያዎች የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ተገለፀ
- በኢትዮጵያ የቴሌኮም ተደራሽነት 54.8 በመቶ ደርሷል- ኢትዮ ቴሌኮም
ተቋሙ ከውጭ ምንዛሬ አገልግሎቶች 164 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል ያሉት ፍሬህይወት የ4G ቴሌሎም አገልግሎት ያገኙ ከተሞች ቁጥርም ወደ 164 ከፍ ማለቱን ገልጸዋል።
በአጠቃላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 72 ሚሊዮን ደርሷል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 34 ነጥብ 3 ሚሊዮን ያህሉ የቴሌብር ደንበኞች ናቸውም ብለዋል።
በ2015 ዓ.ም በቴሌብር የተፈጸመው ግብይት መጠንም 679 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሆኑንም ስራ አስፈጻሚዋ ጠቅሰዋል።
በአዲስ አበባ ካሉ ህንጻዎች ውስጥም 75 በመቶዎቹ በ5G ኔትወርክ መተሳሰራቸም በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።
ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 ዓ.ም 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ብድር ከፍላል ያሉት ስራ አስፈጻሚዋ 21 ቢሊዮን ብር ደግሞ ለመንግሥት ግብር መክፈሉን ጠቅሰዋል።
ድርጅቱ ከውጭ ምንዛሬ አገልግሎቶች 164 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ፍሬህይወት በመግለጫው ላይ ተናግረዋል።