የሞባይል ደንበኞች ቁጥር 54 .3 ሚሊየን መሆናቸውን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታውቋል
የኢትዮ ቴለኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በ2013 በጀት ዓመት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ተደራሽነት 54.8 በመቶ ደርሷል ብለዋል።
በ2013 የኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞች ቁጥር 56.2 ሚሊየን መድረሱን ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፣ ይህም ከእቅዱ 108% ነው፣ ከባለፈው ዓመት የ22% እድገት እንዳለውም ተናግረዋል፡፡
ከእነዚህም የሞባይል ደንበኞች ቁጥር 54 .3 ሚሊየን መሆናቸውን አስታውቀዋል።የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር 25 ሚሊየን ደርሷል፣ ይህም በ95 % እድገት ማሳየቱን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡
የፊክስድ በሮድባንድ ተጠቃሚ ቁጥር 374 ሺህ ደርሷል፣ ይህም 85.4 % እድገት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ፊክስድ ስልክ ተጠቃሚ ቁጥርም 912 ሺህ መድረሱን ነው ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወ/ሪት ፍሬህይወት የተናገሩት።
የቴሌ ብር ተጠቃሚዎች ቁጥርም በ3 ወር ውስጥ 6.5 ሚሊየን መድረሱን እና የ12.7 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የገንዘብ ልውውጥ መካሄዱንም አስታውቀዋል።
ለደንበኞች ጥቁር መጨመር በዋጋ ላይ የተደረገ ማስተካከያዎች ዋነኛው መሆኑን በማንሳት፣ የ4G ኤልቲኢ ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች መጀመርም የበኩላቸውን አስታዋጽኦ ነበራቸው ብለዋል።
ከገቢ አንጻርም ኢትዮ ቴሌኮም በ2013 በጀት 56.5 ቢሊየን ብር ማግኘቱንና ጅህም ከእቅዱ አንጻር ሲታይ፣ 101.7 በመቶ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በውጭ ምንዛሪም 166.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማስገባቱን ያነሱት ወ/ሪት ፍሬ ህይወት፣ ይህም ከእቅዱ 106 በመቶ መሆኑን ጠቅሰዋል።ማህበራዊ ሃላፊነትን በመወጣት በክል እስካሁን 847 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉንም አስታውቀዋል።
በኮሮና ቫይረስ ላይ እየተካዬደ ላለ የምርምር ስራም 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል