![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/12/258-183547-img-20250212-163533-143_700x400.jpg)
ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ አዲስ ሲም ካርድ መሸጡን የገለጸው ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ ደንበኞቹም 80 ሚሊዮን ደርሰውልኛል ብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ እዳ መክፈሉን ገለጸ
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በተቋሙ የስድስት ወራት አፈጻጸም ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 61.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።
ስራ አስፈጻሚዋ አክለውም በስድስት ወሩ በስምንት ከተሞች የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት የተጀመረ ሲሆን 67 ከተሞች ደግሞ የ4ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።
በአጠቃላይ 491 ከተሞች የ4ጂ ኔትወርክ አገልግሎት በማግኘት ላይ እንደሆኑም ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 80.5 ሚሊዮን እንደደረሰ የተናገሩት ፍሬህወት ታምሩ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 6 ሚሊዮን አዲስ ደንበኞች አፍርቷልም ብለዋል።
ቴሌብር የተሰኘው መተግበሪያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የአንድ ትሪሊዮን ብር ግብይት ተፈጽሞበታል የተባለ ሲሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ የቴሌብር ግብይት ሶስት ትሪሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል።
በተጨማሪም ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 23.74 ቢሊየን ብር ታክስ ለመንግስት ገቢ ያደረገ ሲሆን 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ወይም 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የውጭ ብድር መክፈሉንም አስታውቋል።