ፖለቲካ
ፈረንሳይ በባቡር መስመሯ ላይ አሻጥር ከተፈጸመባት ከአንድ ቀን በኋላ ዘራፊዎች የቴሌኮም መስመሯን አጠቁ
ፈረንሳይ ትልቅ ትኩረት የተሰጠውን የፓሪስ ኦሎምፒክ እያስተናገደች ትገኛለች
ይህ ክስተት በባቡር መስመሩ ላይ ከተፈጸመው አሻጥር ጋር ግንኙነት ስለመኖሩ ለመናገር ጊዜው ገና ነው ብለዋል
ፈረንሳይ በባቡር መስመሯ ላይ አሻጥር ከተፈጸመባት ከአንድ ቀን በኋላ ዘራፊዎች የቴሌኮም መስመሯን አጠቁ
ዘራፊዎች በተወሰነ የፈረንሳይ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ የቴሌኮም መስመሮች ሌሊቱን በማጥቃት የመስመር እና የሞባይል አገልግሎቶች ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ ማድደረጋቸውን የዲቲታል ጉዳዮች ሚኒስትር ማሪና ፈራሪ በዛሬው እልት በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል።
ይህ ክስተት ባለፈው አርብ የኦሎምፒክ መክፈቻ ስነስርአት ከመካሄዱ ከሰአታት በፊት በባቡር መስመር ላይ ከተፈጸመው እና ትርምስ እንዲፈጠር ካደረገው አሻጥር ጋር ግንኙነት ስለመኖሩ ለመናገር ጊዜው ገና ነው ብለዋል።
የዘረፋውን ድርጊት "የፈሪዎች ስራ እና ኃላፋነት የጎደለው" ነው ያሉት ፈራሪ አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። ኤስኤፍ የተባለው ቴሌኮም ኦፐሬተር ቃል አቀባይ ዘራፊዎች ሰኞ እለት ጠዋት ረጅሙን የቴሌኮም ኔትዎርክ በአምሰት የተለያዩ ቦታዎች መቁረጣቸውን ገልጿል።
ይህ ድርጊት በደንበኞች ላይ ያደረሰው ተጽዕኖ አነስኛ ነው ብለዋል ፈራሪ።
ሊ ፓሪሴን የተባለው ጋዜጣ ቀደም ሲል እንደዘገበው ከሆነ ኬብሎች በደብባዊ ፈረንሳይ መቆረጣቸውን እንዲሁም በለግዘምበርግ አቅራቢያ በሚገኘው መውዜ ግዛት እና በፓሪስ አቅራቢያ በሚገኘው ኦይሴ አካባቢ ያሉ ጣቢያዎች በዘራፊዎች በመወሰዳቸው ስድስት መስመሮችን አስተጓጉጓል።
ተቋርጦ የነበረው የባቡር መስመር ወደ አገልግሎት የተመለሰው ትናንት ጠዋተ ነው። በባቡር መስመሩ መቋረጥ ምክንያት 800ሺ ሰዎች ከበረራ ተስተጓጉዋል።
ፈረንሳይ ትልቅ ትኩረት የተሰጠውን የፓሪስ ኦሎምፒክ እያስተናገደች ትገኛለች።