የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በምን ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደረሱ?
በመንግስት እና በህወሓት በደቡብ አፍሪካ ሲያደርግ የነበረው የሰላም ንግግር ውጤት ዛሬ ይፋ ተደርጓል
የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ሲካሄድ የነበረው የሰላም ንግግር ዛሬ ተቋጭቷል።
የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የፌደራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ንግግር ይዘት ይፋ አድርገዋል።
በመግለጫቸውም አሁን በኢትዮጵያ የሰላም ንግግር ወደ ሰላም ትግበራ የሚሸጋገርበት ምእራፍ ላይ ደርሷል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ
ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ በጦርነት ላይ የነበሩት የፌደራል መንስት እና ህወሓት በዘላቂነት ግጭት ለማቆም መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ለተቸገሩ ወገኖች ሁሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ
የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነትን ለማረጋጋጥ
አገልግሎቶችን_ለማስጀመር ስምምነት ላይ ከተደረሱባቸው ጉዳዮች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።
በመንግስትና በህወሃት መካከል የተደረሰዉን የሰላም ስምምነት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የህወሓቱ ተወካይ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በፊርማቸዉ አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋንና አቶ ጌታቸዉ ረዳ ስምምነት ላይ የተደረሱባቸዉን ነጥቦች በጋራ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያን ልኡክ የመሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስምምነቱን ከመፈረም ባሻገር ለተግባራዊነቱ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ የሰላም ስምምነቱ መፈረሙን በማድነቅም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ነው የጠየቁት።
የውጭ ሃይላት ሲያደርሱት የነበረውን ጫና በማንሳትም ከዚህ በኋላ ግን ይህ እንደሚስተካከልና የሰላም ጥረቱ ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አለም አቀፉን ህግ መሰረት አድርጋ የውጭ ግንኙነቷን እንደምታሻሽልም ነው አምባሳደር ሬድዋን ያነሱት።
ሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርአትን ለመትከል የጀመረቻቸው የተቋማት ግንባታ ተስፋ ሰጪነትን በመጥቀስም ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክሩ የተለያዩ ቁርሾዎችን ሊፈታ እንደሚችል አብራርተዋል።
ስምምነቱ እንዲደረስ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ተሳትፎ ያደረጉ ተቋማትና ሀገራትንም አመስግነዋል።
የህወሃትን ቡድን ልኡክ የመሩት አቶ ጌታቸው ረዳም ባደረጉት ንግግር፥ ስምምነቱን የአዲስ ነገ ጅማሬ ነው ብለውታል። ከመንግስት ጋር የተደረሰው ስምምነት ለትግራይ ብቻ ሳይሆን ለመላው ሰላም ናፋቂ ኢትዮጵያ ትልቅ ብስራት መሆኑንም አንስዋል።
ይሁን እንጂ ሁለቱም የስምምነቱ ፈራሚዎች ስምምነቱን አክብረው ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ህወሃት ስምምነቱን የፈረመው ለትግራይ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣትና የመልሶ ማቋቋም ስራውም በፍጥነት እንዲካሄድ በማሰብ ነውም ብለዋል።
የትግራይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ፤ በመድሃኒት እጦት ለሚሰቃዩትም መድሃኒት እንዲደርሳቸው በአጠቃላይ ሰላም እንዲረጋገጥ ህወሃት ተኩስ ለማቆም መስማማቱንም አክለዋል።
ሆኖም ባለፉት 10 ቀናት ድርድሩም እየተካሄደ ጦርነቱ መቀጠሉን ጠቅሰው፥ በዚህም በሁለቱም ወገን ዜጎች እየረገፉ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመሆኑም ከረጅም ሂደት በኋላ የተደረሰው ስምምነት የሰላም አየርን እንዲያመጣ ሁለቱም ወገኖች ተኩስ ሊያቆሙ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአፍሪካ ህብረትን የአደሬዳሪነት ሚና በማድነቅም አጋር ሲሉ የገለጷቸው አለም አቀፍ ተቋማትና ሀገራት ለስምምነቱ ተፈፃሚነት ክትትላቸው እንዳይለይ ጠይቀዋል።