ጠ/ሚ ዐቢይ “በደቡብ አፍሪካው ድርድር ኢትዮጵያ ያቀረበችው ሀሳብ 100 በመቶ ተቀባይነት አግኝቷል” አሉ
በደቡብ አፍሪካ ድርድር ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች በመሬት ላይ ያስገኙትን ድል የሚያስረግጥ የሰላም ድል ተገኝቷል
የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች በንግግርና በሀገሪቱ ህግ መሰረት ለመፍታ ከስምምነት መደረሱን አስታውቀዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “በደቡብ አፍሪካው የሰላም ድርድር ኢትዮጵያ ያቀረበችው ሀሳብ 100 በመቶ ተቀባይነት አግኝቷል” አሉ።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ሲካሄድ የነበረው የድርድር ውጤት በትነትናው እለት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
በድርድሩ ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች ውስጥም ግጭትን በዘላቂነት ማቆም፣ ሰብዓዊ እርዳታን ያለገደብ ማድረስ፣ በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት ህግና ስርዓትን ማስከበር አንዲሁም የህወሓት ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታትየሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአርባ ምንጭ ከተማ ”የሌማት ትሩፋት” የተሰኛ ሀገር አቀፍ የእንስሳት ተዋጽዖ ልማት መርሐ ግብርን ማስጀመሪያ ላይ ንግግር አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በንግግራቸውም፤ “ጦርነትን አብዝተን እንጠላለን፤ እኛ የመንፈልገው ሰላም እና ብልጽግናን ነው” ያሉ ሲሆን፤መንግሥታቸው ያገኘውን የሰላም ዕድል እንደሚቀበል ተናግረዋል።
“በደቡብ ፍሪካ የሰላም ድርድር የተገኘው ድል ጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች በመሬት ላይ ያስገኙትን ድል የሚያስረግጥ የሰላም ድል ነው” ሲሉም ጠቅሰዋል።
“ከተገኙ ዋና ዋና ድሎች መካከልም አንደኛው የኢትዮጵያ ሉላዊነትና የግዛት አንድነት ለድርድር አይቀርብም የሚለው በሁለቱም ወገን ተቀባይነት አግኝቷል ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ፤ ሁለተኛው “በአንድ ሀገር ውስጥ ከአንድ መከላከያ በላይ አያስፈልግም የሚለው ጉዳይ ላይም ከስምምነት መደረሱን” አንስተዋል።
በህገ ወጥ መንገድ የተደረገ መርጫ ተሰርዞ በህጋዊ እንዲተካ እንዲሁም ከአንድ አንድ ቦታዎች ላይ ከወሰን ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች የሰው ህይወትን ሳይጠይቁ በሰላም በድርድር እና በሀገሪቱ ህግ መሰረት እንዲፈቱ ከስምምነት መደረሱንም አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በንግግራቸው “በደቡብ አፍሪካው ድርደር ኢትዮጵያ ያቀረበችው ሀሳብ 100 በመቶ ተቀባይነት አግኝቷል” ሲሉም ተናግረዋል።
“የተገኘው የሰላም ድል ለኢትዮጵያ ታላቅ እድል ስለሆነ መላው የኢትዮጵያ ዜጎች ትግራይን እና የትግራይን ህዝብ ለመገንባ እና ወደ ቀደመ የሀገሩ ስሜት ለመመለስ አብረን እንቁም” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
“የኢትዮጵ ጀግንነት የሚረጋገጠው ካለን ላይ በመቀነስ የትግራይ ህዝብነ ማገዝ ስንችል ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ካለን አካፍለን በመስጠት ኢትዮጵያዊነት ምን እንደሆነ ለዓለም ህዝብ ማሳየት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም “ለመላው የትግራይ ሕዝብ ማስተላለፍ የምፈልገው መልዕክት አላስፈላጊ ጦርነት፣ አላስፈላጊ ጉዳት፣ አላስፈላጊ ኢትዮጵያን አሳልፎ መስጠት በዚህ ይብቃ” ብለዋል።
ብዙ ጊዜ ከድርድር በኋላ ሽፍጦች እና ተከንኮሎች ይታያሉ፤ ስለዚህም የተከበርከው የትግራይ ህዝብ እኛ ልባችንን ከፍተን ሰላም ለማምጣት ዝግጁ ስለሆንን ይህንን የገባነውን ቃል ለመጠበቅ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር የብኩልህን ሚና እንድትወጣ ጥሪ አቅርባለሁ” ብለዋል።