አትሌት አልማዝ አያና የአመስተርዳም ማራቶንን የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸነፈች
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ እና አትሌት ፀሃይ ገመቹ የአመስተርዳም ማራቶንን 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል
አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው የአመስተርዳም ማራቶንን የወንዶች ውድድርን አሸንፏል
አመስተርዳም ማራቶን፤ ከትክ ውሰድድር ወጥተው ማራቶንን ለመጀመሪያ ጊዜ የሮጡት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ድል አስመዝግበዋል።
በውድድሩ አትሌት አልማዝ አያና ለመጀመሪያ ግዜ የሮጠችውን የአመስተርዳም ማራቶንን የቦታውን ሪከርድ በመስበር ማሸነፍ መቻሏን ተነግሯል።
አትሌት አልማዝ አያና ውድድሯን በ2: 17:22 በሆነ ሰዓት በመግባት የስፍራውን ክብረ ወሰን በመስበር ውድድሩን ማጠናቀቅ ችላለች።
አትሌት አልማዝ በጉዳት እና በወሊድ ምክንያት ከውድድር ርቃ ቆይታ እንደነበረ ይታወቃል።
በውድድሩ የመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯን ያደረገችው አትሌት ገንዘቤ ዲባባ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀች ሲሆን፤ ሌላኛዋ ማራቶንን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው አትሌት ጸሃይ ገመቹ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
የአለም የ1500 ሜትር ባለሪከርዷ ገንዘቤም ከትራክ ውድድር ወደ ማራቶን ፊቷን መልሳለች።
በወንዶች በተካሄደው የአመስተርዳም ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው የራሱን ሰዓት በማሻሻል ማሸነፍ መቻሉ ታውቋል።
አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው 2.04.49 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ማሸነፍ መቻሉ ተነግሯል።
ኬንያዊው አትሌት ታይተስ ኪፕሩቶ ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው አትሌት ባዘዘው አስማረ 2:04.57 በሆነ ሰዓት በመግባት ሶስተኛ ወጥቷል።