በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ 58 ሜዳሊያዎች ያገኘችው ኢትዮጵያ የፊታችን ሀምሌ በሚካሄደው ፓሪስ ኦሎምፒክ ላይም ትሳተፋለች
በየአራት ዓመቱ አንዴ የሚካሄደው የመላው ስፖርታዊ ውድድር ወይም ኦሊምፒክ የ2024 ውድድር በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ይካሄዳል።
ውድድሩ ከሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ በውድድሩ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል ናት።
በአትሌቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያን በውድድሩ ላይ የሚወክሉ አትሌቶች ምርጫ በስፔን ኔርሀ ባሳለፍነው አርብ ምሽት ተደርጓል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በ10 ሺህ ሜትር ሁለቱም ጾታ፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች እንዲሁም በ800 ሜትር ወንዶች የማጣሪያ ውድድሮች ተካሂደዋል።
ሀገሪቱ አጠቃላይ በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ያላት ታሪክ የሚከተለውን ይመስላል፡፡