ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማካሄድ ከስምምነት ደረሱ
በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል የተደረሱ መግባባቶች ያሉበት ደረጃ ላይ ምክክር አድርገዋል
አቶ ደመቀ ከሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒሲትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ።
አቶ ደመቀ መኮንን ከሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር የተገናኙት በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ነው።
በዙህም በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽፍሀት ቤት አስታውቋል።
እንዲሁም የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ጉብኝ ባደረጉ ወቅት የተደረሱ መግባባቶች ያሉበት ደረጃ ላይ ተነጋግረዋል።
የሁለቱ አገራት የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲካሄድም ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።
የሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ይፋዊ የስራ ጉብኘት ማድረጋቸው ይታወሳል።
በቆይታቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መወያየታቸው ይታወሳል።
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ያለውን ግንኙነት ለመቀጠል ተስማምተዋል።
ሰርጌ ላቭሮቭ የሁለቱ ሀገራት የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ እንዲካሄድ ሩስያ ፍላጎቷ እንደሆነም ገልጸው ነበር።