ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የወደብ ስምምነት ዙሪያ የአቋም ለውጥ አድርጋለች?
የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ ህዝቡን ባሳተፈ መንገድ በውይይት ለመፍታት ጥረት ይደረጋል ተብላል
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ለመሆን የተጀመረው ድርድር በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የወደብ ስምምነት ዙሪያ የአቋም ለውጥ አድርጋለች?
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ፣ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ስለተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እና ሌሎቹም ተጠቃሽ ናቸው።
አቶ ነብዩ እንዳሉት የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ በድንበር አካባቢ ያሉ ማህበረሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መንገድ በሁለቱ ሀገራት በሚዋቀር ኮሚቴ ይፈታል ብለዋል።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር ሊቀየር በማይችል ኹኔታ ለመጨረሻ ጊዜ ተሠምሯል ማለቱ አይዘነጋም።
የኤርትራ ጦር በርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን እንደተቆጣጠር እና አካባቢዎቹን ወደ ኤርትራ ማካለሉን እንዴት ኢትዮጵያ እንዴት ታየዋለች? በሚል ለቃል አቀባዩ ለቀረበላቸው ጥያቄም "ጥያቄው ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የማህበረሰብ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደተነሳ እና ጉዳዩ በውይይት ይፈታል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፣ አሁንም ማለት የምችለው ይህንን ነው" ብለዋል።
ከአራት ወር በፊት በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተካሄደው የወደብ መግባቢያ ስምምነት ጉዳይ ሌላኛው በዛሬው መግለጫ የተነሳ ጉዳይ ሲሆን ኢትዮጵያ ከሶማሊያ እና ሌሎች ሀገራት ባደረሱት ጫና ምክንያት የአቋም ለውጥ ወይም ሌላ አዲስ ነገር ይኖር ይሆን? በሚል ጥያቄ ተነስቷል።
ቃል አቀባዩ በሰጡት ምላሽም " ከሶማሊላንድ ጋር በተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት ዙሪያ የተቀየረ አቋም የለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔት የሚኖሩ 70 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ለመመለስ የተጀመረው ጥረት እንደቀጠለ ነው የተባለ ሲሆን በሳምንት 12 በረራዎች እየተደረጉ እንደሆነም ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብን ለመቀላቀል የጀመረችው ድርድር በጥሩ መልኩ እየሄደ ነው የተባለ ሲሆን በተለይም ምርቶችን በመሸጥ ዙሪያ ጥሩ መሻሻል ሲያሳይ በቀጣይ ደግሞ በንግድ አገልግሎቶች ዙሪያ ተጨማሪ ድርድር እንደሚደረግ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
ከ24 ዓመት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ትስስር ለማሳለጥ የተቋቋመው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጥምረት በየጊዜው አዳዲስ አባላትን በመሳብ ላይ ይገኛል።
ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከአንድ ዓመት በፊት ይህን ጥምረት ለመቀላቀል በይፋ ከጠየቀች በኋላ ባሳለፍነው ሕዳር ወር ጀምሮ ስምነኛዋ አባል ሀገር መሆኗ ይታወሳል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ የ300 ሚሊዮን ህዝብ መገበያያ መድረክ ሲሆን ኢትዮጵያ አባል ከሆነች የአባል ሀገራቱን ቁጥር ወደ ዘጠኝ የግብይት መጠኑንም ከ400 ሚሊዮን በላይ በማድረስ በአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኢኮኖሚ ትስስር ወደ መሆን ይሸጋገራል ተብላል።
በድርቅ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን አንድ ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ለማሰባሰብ በስዊዘርላንድ ጀኔቭ በተካሄደው እርዳታ ላይ የታሰበውን ያህል ገንዘብ መሰብሰብ እንዳልተቻለም ተገልጿል።
በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የታሰበውን ያህል ገንዘብ ማግኘት ያልተቻለው አፍሪካን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች በተመሳሳይ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች እና ተቋማት በመኖራቸው እንደሆነ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።