በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ_19) የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መገኘታቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ_19) የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መገኘታቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡
የመጀመሪያዋ ታማሚ የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን መጋቢት 8/2012 ከብራሰልስ ቤልጅየም እንዲሁም መጋቢት 10/2012 ዓ.ም ወደ ካሜሮን የጉዞ ታሪክ የነበራት ሲሆን ግለሰቧ የበሽታው ምልክት ስለታየባት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ አድርጋለች፡፡ ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ መጋቢት 19/2012 ዓ.ም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል፡፡
ሁለተኛ እና ሶስተኛ ታማሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር፡፡ ግለሰቦቹ መጋቢት 19/2020 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ለተጨማሪ መረጃ ነፃ የስልክ መስመሮችን 8335 ወይም 952 ወይም መደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም የኢሜል አድራሻ ephieoc@gmail.com መጠቀም ይቻላል።