ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ “የመጀመሪያ ቀናችንን በድል ጀምረናል ፍፃሜውም ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ" አለች
በሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግተ አሸንፈዋል
የወንዶች የ10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ዛሬ ምሽት የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ይጠበቃሉ
ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ “የመጀመሪያ ቀናችንን በድል ጀምረናል ፍፃሜውም ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ" አለች።
19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በትናናው እለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም በተሳተፈችበት የመጀመሪያ የፍጻሜ ወድድር ድልን ተቀዳጅታለች።
በሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው የወርቅ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል።
ከፍተኛ ፉክክር በተደረገበት ውድድሩ ጉዳፍ ፀጋይ የወርቅ፣ ለተሰንበት ግደይ የብር እና እጅጋየሁ ታየ የነሀስ ሜዳሊያ በማግኘት አሸንፈዋል።
ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በሰጠችው አስተያየት፤ በተገኘው ድል ደስተኛ መሆኗን ገልጻች።
"ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘን ማጠናቀቅ ችለናል ያለችው ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ፤ "ፈጣሪ ይመስገን የመጀመሪያ ቀናችንን በወርቅም በብርም በነሀስም ጀምረናል ፍፃሜውም ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ” ብላለች።
በዛሬው እለትም ውድድሩ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፤ ምሽት 1:25 ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የወንዶች የ10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።
በሪሁ አረጋዊ ፣ ሰለሞን ባረጋ ፣ ይስማው ድሉ በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ሲሆን፤ ታደሰ ወርቁ በተጠባባቂነት ተይዟል።