ኢኮኖሚ
የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 124 ብር እየገዙ ከ124 እስከ 127 ብር እየሸጡ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው
በህዳር 18 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ስንት ብር ገባ?
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከሁለት ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ቅዳሜ እለት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ቢያስቀጥልም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ በዶላር መግዣው ላይ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጓል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.4134 ብር ገዝቶ በ126.9017 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
አቢሲኒያ ባንክ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትንና የሚሸጥበትን እለታዊ ተመን ይፋ ሲያደርግ አንድ ዶላርን በ123.8647 ብር ገዝቶ 126.3420 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።