በህዳር 17 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ122 እስከ 124 ብር መግዣ ከ124 እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከሁለት ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ቅዳሜ እለት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ቢያስቀጥልም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ በዶላር መግዣው ላይ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጓል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.1965 ብር ገዝቶ በ126.6805 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
አቢሲኒያ ባንክ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትንና የሚሸጥበትን እለታዊ ተመን ይፋ ሲያደርግ አንድ ዶላርን በ123.8647 ብር ገዝቶ በ126.3420 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።
ጸደይ ባንክ የህዳር 17 የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.9558 ብር ገዝቶ በ126.4350 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።