ረቂቅ በጀቱ ከ2015 በጀት የ15 በመቶ ገደማ ጭማሪ አለው
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ የ2016 በጀት 801 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወስኗል።
ከ2015 በጀት ጋር ሲነጻጸር 15 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚበልጠው ረቂቅ በጀቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኳል
አዲሱ በጀት በሰሜኑ ጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከመገንባት አኳያ የተቃኘ ነው ተብሏል።
ሰኔ 30 የሚጠናቀቀው የ2015 ዓመት በጀት 786.6 ቢሊዮን ብር ነው።