የዓለም የባሪያ ንግድ እውነታዎች
20 ሚሊዮን አፍሪካዊያን በባሪያ ንግድ መልክ ተሸጠዋል
ብራዚል እና የካሪቢያን ሀገራት ዋነኛ በባርነት የተሸጡ ዜጎች የተጓጓዙባቸው ሀገራት ናቸው
የባሪያ ንግድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ155 ዓመታት ተተግብሯል።
እንደ ስታስቲካ መረጃ ከሆነ 20 ሚሊዮን አፍሪካዊያን በባርነት ወደ ተለያዩ ሀገራት ተጓጉዘዋል።
ብራዚል፣ ጃማይካ፣ ትሪንዳድ እና ቶቤጎ፣ አሜሪካ እና ፈረንሳይ አፍሪካዊያን በባርነት የተጓጓዙባቸው ሀገራት ናቸው።
የባሪያ ንግድ በፖርቹጋል እንደተጀመረ የሚነገር ሲሆን፥ በናይጀሪያዋ ሌጎስ የመጀመሪያው የባሪያ ሽያጭ ተከሂዷል ተብሏል።
በርካታ የዓለማችን ሀገራት የባሪያ ንግድን በተናጥል በይፋ ያቆሙ ቢሆንም በይፋ የባሪያ ንግድ እንዲቆም የተወሰነው በፈረንጆቹ 1926 ላይ በሊግ ኦፍ ኔሽን ውሳኔ መሆኑ የሚታወስ ነው።
አፍሪካዊቷ ሞሪታንያ የባሪያ ንግድን ለመጨረሻ ጊዜ ያቆመች ሀገር ስትሆን በፈረንጆቹ 1981 ላይ የባሪያ ንግድን ማከናወን እንደማይቻል በይፋ አውጃለች።