85 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ሃብት ያስመዘገቡት ቤተንኮርት ማየርስ ከሴት ቢሊየነሮች ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል
በአለማችን 337 ሴት ቢሊየነሮች እንዳሉ የፎርብስ መረጃ ያመለክታል።
በ2023 የቢሊየነሮችን ዝርዝር ተጨማሪ ስድስት ሴቶች ተቀላቅለዋል።
ፈረንሳዊቷ ፍሬንስፋውዝ ቤተንኮርት ማየርስ ለሶስት ተከታታይ አመታት ከሴት ቢሊየነሮች ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል (በ85 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር)።
ባለፈው አመት ሀብቷ ከ19 ቢሊየን በላይ የቀነሰው አሜሪካዊቷ ማካንዚ ስኮት ደግሞ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ዝቅ ብላለች።
ሶስት ሴት ቢሊየነሮች በፎርብስ አጠቃላይ የቢሊየነሮች ደረጃ እስከ20ኛ ባለው ደረጃ ይገኛሉ።
14 ሴት ቢሊየነሮች በ100 የአለማችን ቱጃሮች ዝርዝር ውስጥ መግባት መቻላቸውንም መረጃው ያሳያል።