በዓሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከበረ ነው
126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዛሬው እለት በተላያዩ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
የዘንድሮው የድል በዓል “ዐድዋን ለኢትዮጵያውያን ኅብረት፣ ለአፍሪካ የነፃነት ጮራ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የሀገሪቱ ከክፍሎች በመከበር ላይ ይገኛኛ።
በዓሉን ምክንያት በማድረግም በአዲስ አበባ ንጋት ላይ መድፍ ተተኩሷል።
በዓሉ በአዲስ አበባ ሚኒሊክ አደባባይ ላይ አባት እና እናት አርበኞች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች እንዲሁም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።
በዝግጅቶቹ ላይ ዳግማዊ አጼ ምኒልክን፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ (አባ ነፍሶን) እንዲሆም የወቅቱን ኢትዮጵያውያን አርበኞች የሚዘክሩ ትዕይንቶች ተስተውለዋል።
በበዓሉ ላይ አርበኞች ፉከራ እና ሽለላን በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀትን ሰጥተዋል።
የአድዋ የድል በዓል በአዲስ አበባ አድዋ ድለድይም በተለያ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያውያን በአጼ ሚኒሊክ እየተመሩ ቅኝ ሊገዛ የመጣውን የፋሽት ወራሪ ኃይል በ1888 ዓ.ም አድዋ ላይ ድል አድርገው በመላው ጥቁር ህዝብ ድልነት የሚጠቀስ አዲስ ታሪክ መጻፋቸው የሚታወቅ ነው።