ልዩልዩ
በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ደረሰ
ለመጀመሪያ ጊዜ በቫይረሱ ከተያዘው ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ 2 ጃፓናዊያን እና አንድ ኢትዮጵያ ከአሁን ቀደም በቫይረሱ ተይዘዋል መባሉ የሚታወስ ነው
5ኛው ከዱባይ የመጣ ግለሰብ ነው
በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ደረሰ
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት ተዘግተው እንደሚቆዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡
ወረርሽኙን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሁን ላይ 5 መድረሳቸውን ጠቅሰው 5ኛው ግለሰብ ከዱባይ የመጣ መሆኑንም አስቀምጠዋል።
ይህም በቫይረሱ የተያዙ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር 2 የሚያደርስ ነው፡፡
ክትትል እየተደረገለት ከሚገኘው ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ከነበራቸው ሰዎች መካከል ሁለት ጃፓናዊያን እና አንድ ኢትዮጵያ በቫይረሱ መያዛቸውን ጤና ሚኒስቴር ማረጋገጡ የሚታወስ ነው፡፡