ኢትዮጵያ የኢጋድ ሊቀመንበሯ ሱዳን የአፍሪካ ቀንድ ሰላምን አደጋ ላይ መጣሏን ገለጸች
ሚኒስቴሩ አለምአቀፉማህበረሰብ በሰዱን ላይ ጫና ማሳዳደር አለበት ብሏል
የኢትዮጵያ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ሱዳን “ኢትዮጵያን በመውረር” የአፍሪካ ቀንድን ሰላም አደጋ ላይ መጣሏ “የሚያጸጽት ነው” ስትል ገልጻለች
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊትር ገጹ እንደጻፈው “ሱዳን የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የበይነ መንግስታት ድርጅት ሊቀመንበር ሆና” ሳለች በኢትዮጵያ ላይ ወረራ መፈጸሟ የሚያጸጽት ነው ብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ ሰዱን “ኢትዮጵያን በመውረር፣ ንጹሃንን በማፈናቀልና ተጨማሪ መሬቶችን ለመውረር የጦርነት ከበሮ በመምታት የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነትን አደጋ ላይ ጥላለች” ሲል ገልጿል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አለምአቀፉ ማህረሰብ ከፈረንጆቹ ህዳር 6 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህግ ማስከበር ዘመቻ ተወጥሮ በነበረበት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የገባውን ጦሯን እንድታሶጣ በሱዳን ላይ ግፊት ማሳደር እንዳለበት አስፍሯል፡፡
ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ የሱዳን ጦር ወደነበረበት ከተመለሰ በኋላ የድንበሩን ገዱይ በድርድር ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡
“ሱዳን የኢትዮጵያን ልዑላዊ መሬት በወረራ መያዟን ተከትሎ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድርጊቱን በይፋ አለማውገዙ የሚያሳዝን” መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በቅርቡ ለአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኛው ሀቬስቶ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ አለመግባቷንና ጦሯም በራሳ ግዛት እንደሚገኝ በመግለጽ የኢትዮጵያ ክስ ተቀባይነት የለውም ማለቷ ይታወሳል፡፡