የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ 1 ዶላር በ101 ብር እገዛ፤ በ111 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ከካሳለፍነው ጀምሮ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ ከ50 ብር በላይ ጭማሪ ታይቷል።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 4 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 7 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዛሬው እለት 1 የአሜሪካ ዶላርን በ108 በር እየገዛ በ115 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.1287 ብር እየተገዛ በ116.6242 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በአቢሲኒያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ103.0102 ብር እየተገዛ በ115.3714 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
በወጋገን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ103.4984 ብር እየተገዛ በ115.9281 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በዳሽን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ103.7889 ብር እየተገዛ በ115.2057 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከግል ባንኮች ዝቅ ያለ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አውጥቷል። ባንኩ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.8041 ብር እየገዛ በ111.9845 ብር እየሸጠ ነው።