ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጃክ ማ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የቁሳቁስ እርዳታ ተቀብለው ለአፍሪካ ሀገራት ለማከፋፈል ኃላፊነት ወሰዱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጃክ ማ እርዳታ ተቀብለው ለአፍሪካ ሀገራት ለማከፋፈል ኃላፊነት ወሰዱ
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ከቻይናዊው ቢሊየነር ጃክ ማ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን ተቀብለው ለ54ቱም የአፍሪካ ሀገራት ሊያከፋፍሉ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ሀላፊነት ወስዳ እንድታከፋፍል የተደረገው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከ ጃክ ማ ጋር የስልክ ውይይት አድርገው፣ የኮሮና ቫይረስን (የኮቪድ-19) ን ስርጭት ለመግታት የትብብር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ጃክ ማ “ለአፍሪካ ሀገራት ለእያንዳንዳቸው 20 ሺ የመመርመሪያ ኪቶችን፣ 100 ሺ ማስክ እና አንድ ሺ የመድሃኒት መያዣዎችንና የፊት መሸፈኛዎችን ለመለገስ መወሰናቸውን” በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
የጃክ ማ ፋውንዴሽን ባወጣው መግለጫ ጃክ ማ “ በድምሩ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን የመመርመሪያ ኪቶች፣6 ሚሊዮን የፊት ማስክ እና 60 ሺ የመድሃት መያዣዎችና የፊት መሸፈኛዎች ለመለገስ የወሰኑ ሲሆን እነዚህን የመከላከያ ቁሳቁሶች ኢትዮጵያ እንድታከፋፍል ሃላፊነት ተሰጥቷታል” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሀላፊነቱን ለመውሰድ ከጃክ ማ ጋር መስማማታቸውን መግለጫው አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የጃክ ማ በውይይታቸው ወቅት ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
- ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች የሚላኩት መገልገያዎች ዝርዝር እና ብዛት፣
- የአላላክ ዝርዝር እና የሰነድ አያያዝ
- የማከማቻ ሁኔታ እና ወደየአካባቢው የማጓጓዝ ሂደት
- የቫይረሱን ስርጭት ስለመግታት የሚያወሱ አጫጭር መረጃዎች (ወደየአካባቢው ቋንቋ ይተረጎማሉ)
- የሰው ኃይል ጉዳዮች
- የዳታ እና ኢንፎርሜሽን መለዋወጫ መንገዶች ላይ በቴሌኮንፍረንስ ዝርዝር ጉዳዮችን ተነጋረዋል ብሏል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
ቢሊየነሩ ጃክ ማ በተመሳሳይ ለአሜሪካ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆን የመመርመሪያ መሳሪያና 1 ሚሊዮን የፊት መሸፈኛ እንደሚሰጥ ባፈው እሁድ ማስታወቅ የሚታወስ ነው፡፡
ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መጋቢት 4፣ 2012 በሰጡት መግለጫ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው መኖሩን ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ግለሱቡ ጃፓናዊ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የገባው የካቲት 25 መሆኑንና ከእሱ ጋር ንክኪ ያላቸው 25 ሰዎች ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረስ ተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ደርሷል፡፡
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዛሬ ባወጣው “ሽታውን ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት የመጡ ተጓዞችን በተጨማሪ በኮረና ቫይረስ መያዛቸውን ማረጋገጥ ከተቻለው 5 ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸውን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት (992) ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት የሚደረግ የጤና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት አንድ ሺ ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት (1285) የሚሆኑት ደግሞ ለ 14 ቀን የጤና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ጤንነታቸው በመረጋገጡ የጤና ክትትላቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡”
“በሽታው ተመሳሳይ ምልክቶች በማሳየታቸው እንዲሁም ከመጀመሪያው ታማሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸውን ጨምሮ በአሁኑ ሰዓት አንደ መቶ አስራ ሰስት (113) ተጠርጣሪዎች በተለያየ ጊዜ በለይቶ መቆያ ማእከል እንዲቆዩና የላብራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ሰባ አራቱ (74) ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፤ አምስቱ ( 5) የኮሮና ቨይረስ የተገኘባቸው ታማሚዎች ሲሆኑ በለይቶ ማቆያ የህክምና መስጫ ማዕከል የቅርብ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ሰላሳ አራቱ (34 ) ተጠርጣሪዎች በለይቶ ማቆያ ሆነው የለቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡”
ከቻይና ውሀን ግዛት የተነሳው የኮሮና ቫይረስ መላው ዓለምን አዳርሷል፡፡ ቫይረሱ እስካሁን ከ5,000 በላይ ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን 170,000 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡