ኢትዮጵያ በ5 ወራት ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 1.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታወቀች
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ወደ ሀገር ቤት ከመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በአዲስ አበባ ምክክር አካሂዷል
ጨርቃ ጨርቅ፣ ግብርናና ሌሎች ተያያዥ ዝርፎች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የተሳበባቸው ናቸው
ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አንድ ሚሊየን ትውልደ ኢትዮጵያውን እና ኢትዮጵያዊያን ለገና እና ጥቅምት ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ጥሪ ባቀረቡት መሰረት ወደ ሀገር ቤት በመምጣት ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ወደ ሀገር ቤት ከመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በአዲስ አበባ በመምከር ላይ ይገኛል።
ዳያስፖራዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ሚኒስትሮች፣ የክልል ኢንቨስትመንት ቢሮዎች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ዳያስፖራዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የጤና ጥበቃ፣ ትራንስፖርት፣ ኢንዱስትሪ እና ንግድ ሚንስትሮች በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከዚህ መድረክ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ 1. ነጥብ 34 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳቧ ተገልጿል።
ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት፣ ግብርና፣ ኮንስትራክሽን፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ሌሎች ተያያዥ የኢንቨስትመንት ዝርፎች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የተሳበባቸው መስኮች ናቸው።
በዚህ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት መድረክ ላይ ከ800 በላይ ዳያስፖራዎች መሳተፋቸውን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።