የጦርነት ኢኮኖሚ ምን ዐይነት ነው?
“ጦርነት ከሰብዓዊ እና ከሌሎች ማህበራዊ ጉዳቶቹ ባሻገር ምጣኔ ሃብትን ያዳሽቃል”- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን
የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰሩ በጦርነት ወቅት ምናልባትም ለመሳሪያ ግዥ የሚወጣው ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ይናገራሉ
በኢትዮጵያ ላለፉት 13 ወራት የዘለቀው ጦርነት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳቶችን አድርሷል፡፡ ሃገራዊ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎችን ከማቀዛቀዝና እንዲቆሙ ከማድረግም በላይ ክፉኛ ጎድቷል፡፡
በተለይ ጦርነቱ በተካሄደባቸውና በመካሄድ ላይ ባለባቸው አካባቢዎች ያለው ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ ከመገታትና ከመቆምም በላይ ሊያንሰራራ የሚችልባቸውን መሰረተ ልማቶች ጭምር አጥቷል፡፡
በላብ የተገነቡ ከተሞች፤ የጤና ተቋማትንና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ መንገድ፣ ውሃና መብራትን መሰል የህዝብና የመንግስት ሃብት ፈሰስ የተደረገባቸው መሰረተ ልማቶች ወድመዋል፡፡
ህወሓት ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች በሚገኙ የቱሪዝም ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን መንግስት አስታወቀ
ለወትሮው በተለያዩ የንግድና የአገልግሎት እንቅስቃሴዎች ደምቀው ይስተዋሉ የነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች ዛሬ እንደወትሮው መሆን ተስኗቸው በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ ሆነው ይገኛሉ፡፡
በጥረታቸው ከራሳቸው አልፈው ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር፣ ብዙዎችን ለመደገፍና የስራ እድል ለመፍጠር የተሻለ ኃብትን ለማካበት ጭምር ችለው የነበሩ በርካቶች ዛሬ ተወልደው ያደጉበትን፣ ሰርተው ያፈሩበትን ቀዬ ለቀው ለመሰደድና የነበራቸውን ሃብት አጥተው ተጠዋሪ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡
ይህ የጦርነት አስከፊ ገጽታ ነው “ጦርነት ከሰብዓዊ እና ከሌሎች ማህበራዊ ጉዳቶቹ ባሻገር ምጣኔ ሃብትን ያዳሽቃል” እንደሚሉት እንደ የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰሩ መንግስቱ ከተማ ገለጻ፡፡
አዲሱ መንግስት የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር ካልቻለ ሀገር ችግር ውስጥ ትገባለች- አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ
የጦርነት ኢኮኖሚ ምን ዐይነት ነው? በጦርነት ውስጥ ያለ ሃገር ኢኮኖሚስ እንዴት ባለ መንገድ ሊያገገግምና ሊያንሰራራ ይችላል? በሚል ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕሮፌሰር መንግስቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን (EEA) ዋና ስራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡
በጦርነት ወቅት ጦርነቱ ባይኖር የማናወጣቸውን ቀላል የማይባሉ ወጪዎች እናወጣለን የሚሉት ፕሮፌሰር መንግስቱ “እንደ ቤተሰብ እንደ ሃገር የሚታጣው ቀላል አይደለም” ሲሉ ይናገራሉ፤ ለመሳሪያ ግዥ የሚወጣው ምናልባት ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ በመጠቆም፡፡
ፕሮፌሰሩ የጦርነትን አውዳሚነትና ምጣኔ ሃብታዊ መልኩን ሲያስረዱ የጤና፣ የትምህርትና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች ይወድማሉ፤ አሁን እያጣን ነው እነሱን መልሶ ለመገንባት የሚጠይቀው ወጪ ቀላል አይደለም ይላሉ፡፡
አሁን ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ዝቅተኛው የተቀጣሪ ደመወዝ ለጊዜው 6 ሺህ 800 ብር መሆን አለበት- የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
ሌላው በጦርነት የሚሳተፈው በተለይ ወጣቱ ጦርነቱ ባይኖር ኢኮኖሚውን የሚደጉም ነበር፡፡ ሆኖም ጦርነቱ ላይ በመሰማራቱ፣ በመጎዳቱና በመሞቱ ለኢኮኖሚው ብክነት ነው ያገኝ የነበረውንም ያጣል፡፡ ይህ እንደ ቤተሰብ እንደ ሃገር የሚታጣው ቀላል እንዳይደለ ያሳያል፡፡
ተፈናቃዮችንና የጸጥታ አካሉን ጭምር ለመደገፍ የሚውለው ለሌሎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ሊውል ይችል የነበረ ነው፡፡
በጦርነቱ ምክንያት ባጋጠሙ ዲፕሎማሲያዊ ችግሮች ምክንያት ከሃገራት ጋር የነበሩ የንግድ ግንኙነቶች እስከመቋረጥ ጭምር ደርሰዋል፤ አጎአ ለዚህ ማሳያ ነው እንደ ፕሮፌሰሩ ገለጻ፡፡
ኢትዮጵያ ከአሜሪካው አጎአ እንድትወጣ “የሚጎተጉቱ”ት እነማን ናቸው?
በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች ጦርነቱ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ከሚገኙ ወጣቶች ላይ እየደረሱ አይደለም የሚሉት የምጣኔ ሃብት ምሁሩ “ይህ ምናልባት የትውልድ ክፍተት ሊፈጥር የሚችል ነው” ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
ሃገሪቱ በኮሮና ወረርሽኝ ውስጥ የምትገኝ መሆኑ ወትሮውኑ ከነበረው ዝቅተኛ የእድገት ደረጃዋ ጋር ተደማምሮ ለጉዳት እንደዳረጋትም ይገልጻሉ፡፡
ጦርነቱ በዘለቀባቸው ከአንድ ዓመት በበለጡ ወራት ውስጥ ያደረሰው ምጣኔ ሃብታዊ ውድቀትና ኪሳራ ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ሆኖም ውድመቱን በገንዘብ ተምኖ ለማስቀመጥ ጥልቅ ጥናቶች ያስፈልጋሉ፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ አሶሴሽኑ ውድመቶቹን በተመለከተ ለይቶ ያስቀመጠው ነገር እንዳለ የተጠየቁት ዋና ስራ አስፈጻሚው እስካሁን የተቀመጠ ነገር እንደሌለ ነገር ግን ውድመቱን በውል ለማወቅ የሚያስችል ጥናት የማካሄድ እቅድ እንዳለ ነግረውናል፡፡