ከ50 በመቶ በታች ላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች 'የአቅም ማሻሻያ' የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ
ማሻሻያው ፈተና የተሰጠበትን አግባብና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚተገበር ነው ተብሏል
እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 'የአቅም ማሻሻያ' ተጠቃሚ ይሆናሉ
ትምህርት ሚንስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሪድሚያል) የተባለ መርሀ-ግብር ከ50 በመቶ በታች ላመጡ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ይፋ አደረገ።
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርትን ለመከታተል 'የማሻሻያ' የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።
በመርሀ-ግብሩ ተጠቃሚ የሚሆኑት በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከ50 ከመቶ በታች ያላመጡ ተማሪዎች ናቸው።
በተጨማሪም ፈተና የተሰጠበትን አግባብና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት ለአንድ ጊዜ ብቻ ያገለግላል የተባለ የአቅም ማሻሻያ እንዲተገበር ተወስኗል ነው የተባለው።
በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው የዚህ መርሀ-ግብር ተጠቃሚ የሚሆኑ ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ናቸው ተብሏል።
ይህም ማለት ከ700፤ 210 ፣ ከ 600፤ 180 እና ከ 500፤150 ሆኖ ተቆርጧል።