የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
በ2014 ዓ.ም ከ900 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል
ተፈታኞች ከሌሊቱ 5:30 ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
በኮሮና ቫይረስ፣ ጦርነት እና ሌሎች ገፊ ምክንያቶች ዘግይቶ የተሰጠው የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም መሰረት ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ውጤታቸውን በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን ብቻ በመላክ እእንዲሁም በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot
ማየት ትችላላችሁ ሲል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።
ተፈታኞች ከፈተናው ጋር በተያያዘ ማንኛውም ቅሬታ ካላቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።
በ2014 ዓ.ም ከ900 ሺህ በላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወሳል።
ኩረጃን ለመቀነስ ሲባልም ተፈታኞቹ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ፈተናውን መውሰዳቸው አይዘነጋም።