ከ12 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተናን እንዳልወሰዱ ተገለጸ
የ2014 የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና መጠናቀቁ ተገልጿል
ፈተናውን አንፈተንም በሚል ላቋረጡ ተማሪዎች ሁለተኛ እድል እንደማይሰጥም ትምህርት ሚንስቴር ገልጿል
ከ12 ሺህ 700 በላይ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተናን እንዳልወሰዱ ተገለጸ።
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ባሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ መሰጠት የጀመረ ሲሆን ዛሬ ተጠናቋል ተብሏል።
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ስለ ፈተናው በሰጡት መግለጫ 595 ሺህ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተናን መውሰድ ያለባቸው ቢሆንም 585 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።
በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውንም ሚንስትሩ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል።
ፈተናውን አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥም አሳውቋል።
በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ህይወቱ አልፏል።
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቁን ሚንስትሩ አክለዋል።
በፈተናው ወቅት ከሌሎቹ በተለየ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ በደረሰ ግርግር የአንድ (ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት እንደደረሰም ተገልጿል።
በሑዋሳ ዩንቩርሲቲም በመሸጋገሪያ ድልድይ ላይ በተፈጠረ የመደርመስ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል መጉደል አደጋም ደርሷል።
የሁለተኛው ዙር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር ይጠበቃል።