ብሄራዊ ባንክ በሩብ አመት ውስጥ የ2.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ንግድ ጉድለት ማጋጠሙን ገለጸ
የብሄራዊ ባንክ ገዥው የውጭ ምንዛሬ በ5.7 በመቶ ማደጉን በመግለጫው አንስተዋል
ጉድለቱ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ400ሚሊዮን ዶላር ቅናሸ ማሳየቱን ዶ/ር ይናገር ገልጸዋል
ጉድለቱ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ400ሚሊዮን ዶላር ቅናሸ ማሳየቱን ዶ/ር ይናገር ገልጸዋል
ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 2.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ንግድ እጥረት አንዳጋጠማት ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡
የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሩብ አመቱ ያጋጠመው የውጭ ንግድ ጉድለት ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ400ሚሊዮን ዶላር ቅናሸ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ይናገር የውጭ ንግድ ከፍተኛ ቁጥጥር መደረጉ የንግድ ሚዛን መዛባቱን ለመቀነስ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የውጭ ንግድ እድገት መመዝገቡንም በንግድ ሚዛኑ ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳደሩንም ዶ/ር አብራርተዋል፡፡
የብሄራዊ ባንክ ገዥው የውጭ ምንዛሬ በ5.7 በመቶ ማደጉን በመግለጫው አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ከፍ ለማድረግ የብርን የመግዛት አቅም ዝግ ስታቀደርግ መቆየቷን ገዥው አስታውቀዋል፡፡
የዶላር መጠንን ለመጨመር ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ዲፕሎማቶችና ኢትዮጵያውያን የዶላር አካውንት እንዲከፍቱ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 55 ቢሊዮን ብር ብድር የተሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85% የሚሆነው ለግል ዘርፍ የተሰጠ ብድር ነው ብለዋል ዶ/ር ይናገር፡፡
ኢትዮጵያ ስትጠቀምባቸው የነበሩትን የብር ኖቶች የቀየረች ሲሆን ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት የተቀመጠው ከባንክ ውጭ የሚንቀሳቀሰው ብር ወደ ባንክ ስርአት ለማስገባት ነው የሚል ነበር፡፡