የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የቀድሞው ጠ/ር ኃይለማርያም ስለድንበር የተናገሩት ተዛብቶ መቅረቡን ገለጸ
ኢትዮጵያ ከአጤ ምኒልክ ጀምሮ የተፈረሙ ስምምነቶችን ትቀበላለች ብሏል ሚኒስቴሩ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2006 ዓ.ም ስለድንበር ጉዳይ የተናገሩትና የሱዳንን የይገባኛል ጥያቄ ያረጋግጣል የተባለው ንግግር “እውነት” አለመሆኑን ሚኒስቴሩ ገለጸ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአል ዐይን ኒውስ በላከው መግለጫ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በ2006 ዓ.ም በተወካዮች ም/ቤት ፊት ስለኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ተናገሩት ተብሎ በሚያዲያ የሚሰራጨውና የሱዳንን የይገባኛል ጥያቄ ያረጋግጣል የተባው ንግግር “እውነት” አይደለም ብሏል፡፡
በለፈው ሳምንት ሚዲያዎች የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የኢትዮጵያ “ሽፍታዎች”ሱዳን ውስጥ ገብተው ማጥቃታቸውን አምነዋል የሚል ይዘት ያለው መልእክት አሰራጭተው ነበር፡፡
ነገርግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ለማለት የፈለጉት ይህን እንዳልሆነና ከዚህ በተቃራኒ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያውያንና በእርሻቸው ላይ ስለሚደርሰው ጥቃት ከምክርቤቱ አባላት ስለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክርቤቱ አባላት ፍትሃዊ መሆን እንደሚገባና ጥቂት ኢትዮጵያውያን በሱዳኖች ላይ የሚሰሩትን አጉል ተግባር ማየት እንደሚገባና ጣት መጠቋቆም ሰለም እንደማያመጣ ነበር ያብራሩት ብሏል መግለጫው፡፡
ሱዳን ውስጥ ያርሳሉ ስለተባሉት ኢትዮጵያውን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማለት የፈለጉት ባልተመዘገበ ቦታ የሚያርሱትን ለማለት ፈልገው መሆነን መግጫው አብራርቷል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአጤ ሚኒልክ ጀመሮ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የፈረመቻቸው የድንበር ስምምነቶችን ገዥነት እንደምትቀበል ጠቅሷል፡፡ መግለጫው ኢትዮጵያ በእነዚህ ስምምቶች መሰረት ድንበሩ እንዲካለል ስትጠይቅ መቆየቷን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ሱዳን ኃይል ከጥቅምት 27 ጀምሮ ድንበር ጥሳ መግባቱንና ወደ ነበረበት ተመለሶ የድንበር ድርድር እንዲቀጥል ቅደመ ሁኔታ አስቀምጣለች፡፡ ነገርግን እስካሁን ሱዳን ግን ለመመለስ ፍቃደኝ አልሆነችም፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ “ህግ ለማስከበር” በተሰማራበት ወቅት፣ሱዳን የተፈጠረውን ክፍተት ተጠቅማ ወረራ መፈጸሟን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ገልጿል፡፡