የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ በዱባይ ኤክስፖ ሲቲ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ አስጎብኝተዋል
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ እያከናወነች ያለው ስራ ለእይታ ቀርቧል
28ኛው የአለም አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በዱባይ ሲጀመር ኢትዮጵያም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የምታከናውናቸውን ተግባራት ለእይታ አቅርባለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ/ፓቪሊዮን/ ከፍተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የአየር ጸባይ ለውጥን ለመቀነስ በተለይ በአረንጓዴ አሻራ በቢሊየን የሚቆጠሩ ዛፎችን መትከሏን አብራርተዋል።