ለኮፕ28 ስብሰባ የአለም መሪዎች ወደ አረብ ኢምሬትስ እያመሩ ነው
በስብሰባው ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሰሯቸውን ስራዎች ሪፖርት ያቀርባሉ
አረብ ኢምሬትስ ኮፕ 28 በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት በአለም ስኬታ የሆነ ስብሰባ ይሆናል የሚል ተስፋ አላት
ለኮፕ28 ስብሰባ የአለም መሪዎች ወደ አረብ ኢምሬትስ እያመሩ ነው።
በፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነሀያን የቀረበላቸውን ጥሪ ተከትሎ በኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ለመሳተፍ የአለም መሪዎች እና ተወካዮቻቸው ወደ አረብ ኢምሬት እያመሩ ይገኛሉ።
የቶጎ ፕሬዝደንት ዶክተር መሀመድ ፋኡሬ ጊናስንግቤ፣ የጉያና ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዶክተር መሀመድ ኢርፋን አሊ እና የኮትዲቮር ፕሬዝደንት አላሳኔ ኦታራ በትናንትናው እለት አረብ ኢምሬትስ ገብተዋል።
በተጨማሪም የጊኒ ቢሳው ፕሬዝደንት ጀነራል ኦማር ሲሶኮ ኢምባሎ፣ የጋቦን የሽግግር ፕሬዝደንት ጀነራል ንጉይማ እና የፖኪስታን የሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር አኑዋር ሀቅ ካካርም አረብ ኢምሬትስ ደርሰዋል።
በዱባይ ከህዳር 30-12 ለሚካሄደው የአየር ንብረት ጉባኤ መሪዎች መምጣታቸውን ቀጥለዋል።
አረብ ኢምሬትስ ኮፕ 28 በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት በአለም ስኬታ የሆነ ስብሰባ ይሆናል የሚል ተስፋ አላት።
በስብሰባው ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሰሯቸውን ስራዎች ሪፖርት ያቀርባሉ።
ከፖሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ቀጥሎ በሚካሄደው በዚህ ትልቅ ስብሰባ ከሀገራት መሪዎች በተጨማሪ አለምአቀፍ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ወኪሎች በመገኘት መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠቃል።