ከድጎማ ውጪ ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም መግባቱም ተመላክቷል
የኢትዮጵያ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ዛሬ ይፋ በተደረገው እና ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ የሚተገበረው የዋጋ ጭማሪ ዝቅተኛ ገቢ ላለው ሕብረተሰብ የሚሰጠው ድጎማ እንዲጨምር ተደርጓል።
በዚህም መሰረት በድጎማ ሲሸጥ በነበረው በአንድ ሊትር ቤንዚን ከብር 15 ከ 76 ሳንቲም ወደ ብር 17 ከ 33 ሳንቲም እንዲሁም የአንድ ሊትር ናፍጣ ከብር 19 ከ 02 ሳንቲም ወደ ብር 22 ከ 68 ከፍ እንዲል መደረጉ ነው የተገለጸው።
ከድጎማ ውጪ በሶስተኛ ዙር ጭማሪ
ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም
ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ብር ከ 30 ሳንቲም
ኬሮሲን በሊትር 67 ብር ከ30 ሳንቲም ሆኗል፡፡
ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ67 ሳንቲም፣
ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 48 ብር ከ70 ሳንቲም
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 67 ብር ከ91 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።
የዋጋ ጭማሪው ዛሬ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።
የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ በሚመለከት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሕዝብ ማስታወቂያ እንዳዘጋጀ እና በዚሁ የሕዝብ ማስታወቂያ የተካተቱ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገው ዕለት (ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም) ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጿል።