የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የነዳጅ ዋጋ በአውሮፓና በሌሎች የዓለም ክፍሎች አንዲንር አድርጓል
የነዳጅ ዋጋ መናር ያስመረረው ፈረንሳያዊው ግለሰብ ወደስራ ለመሄድ ፈረስን ለመጠቀም እንዳስገደደው ይናገራል።
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የፈጠረ ሲሆን፤ የነዳጅ ዋጋ ላይ የታየው ጭማሪም የዚሁ አካል ነው።
አውሮፓም የዋጋ ግሽበት ካጋጠማቸው ውስጥ አንዷ ስትሆን የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት አስቸጋሪ ሁኔታ እንደገጠማት ይነገራል።
በርካታ አውሮፓውያን ለመኪኖቻቸው ነዳጅ መግዣ አቅም ማጣታቸው እየተነገረ ሲሆን፤ በዚህም የተነሳ አማራጮችን መጠቀም ግድ እየሆነባቸው መምጣቱም ተመላክቷል
የነዳጅ ዋጋ መናርን ተከትሎ ለመኪናው ነዳጅ መቅጃ አቅም ያነሰው ፈረንሳያዊው ሉዊስ ጄኔክስም አማራጭ የመጓጓዣ መንገድ መፈለግ የግድ እንዳለውም ታውቋል።
እንደ ኦስትሪያው ቴሌቪዥን ዘገባ ሉዊስ ጄኔክስ አሁን ላይ ወደ ስራ ለመሄድም ሆነ ከስራ ወደ ቤቱ ለመመለስ ፈረስን መጠቀም ጀምሯል።
ምክንያቱም በአሁን ጊዜ መኪናውን ነዳጅ ለመሙላት 100 ዩሮ ያስፈልገዋል ይህንን ለማድረግ ደግሞ አቅም እንዳነሰውም ሉዊስ ጄኔክስ ይናገራል።
ከዚህ የተነሳም ሉዊስ ጄኔክስ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ ፈረስን በመጠቀም ለነዳጅ የሚያወጣውን ወጪ ለመቆጠብ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
ሉዊስ ጄኔክስ ወደ ስራው ለመሄድ 15 ኪሎ ሜትሮች የሚጓዝ ሲሆን፤ በፈረስ አንድ ሙሉ ሰአት እንደሚፈጅበት እና በመኪና ግን ቢበዛ 10 ደቂቃ ይፈጅ እንደነበር ይናገራል።
ሉዊስ ጄኔክስ ፈረሱን በአስተናጋጅነትበሚሰራበት ሬስቶራንት እንደሚያቆየውና በየጊዜው እንደሚጠብቀው ይናገራል።
አሌክስአንደር ሌንሀርት የተባለ አስተያየት ሰጪ፤ “ከ50 ዓመታት ሰዎች በመኪና ፈጣን መሆኑን አስበው ነበር የፈጠሩት፤ አሁን ግን ተመልሰን በፈረስ መጓጓዝ ጀምረናል ምክንያቱም መኪኖች በአሁን ሰአት ውድ በመሆናቸው ነው” ብሏል።