አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ የተበረከተላቸውን 2 ሚሊየን ብር “ለእኔ እንደ ስድብ ስለሆነ መመለስ እፈልጋለሁ” አሉ
አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ በፓሪስ ኦሎምፒክ ማራቶን የወርቅና የብር ሜዳሊያ ያመጡት አትሌቶች አሰልጣኝ ናቸው
አሰልጣኙ ከመንግስት የተበረከተላቸው ገንዘብ “ልፋታችንን አይመጥንም” ብለዋል
የማራቶን አትሌቶች አሰልጣኝ የሆኑት አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ የተበረከተላቸውን 2 ሚሊየን ብር “ለእኔ እንደ ስድብ ስለሆነ መመለስ እፈልጋለሁ” አሉ።
በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑክ ቡድን በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል እና የእራት ግብዣ ተደርጎለታል።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በተካሄደው የአቀባበል እና የአውቅና ስነ ስርዓት ላይም ለአትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና ለታሳታፊዎችዎች እንደየ ተሳትፏቸው እና አብርክቷቸው ከ50 ሺህ ብር እስከ 7 ሚሊየን ብር የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል።
በዚህ ስነ ስርዓት ላይ በማራቶን ለኢትዮጵያ ብቸኛውን ወርቅ ሜዳሊያ ላስገኘው አትሌት ታምራት ቶላ 7 ሚሊየን ብር እና ወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል።
የብር ሜዳልያ ላመጡት አትሌት ትግስት አሰፋ፣ አትሌት በሪሁን አረጋዊ እና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለእያንዳንዳቸው የ 4 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የታምራት ቶላ እና ትግስት አሰፋ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ በስነ ስርዓቶ ላይ የ2 ሚልዮን ብር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፤ መድረክ ላይ ከቀረቡ በኋላ ሽልማቱን ለመውሰድ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ በመድረኩ ላይ ከመድረክ መሪዎችች ማይክራፎን ተቀብለው ባደረጉን ንግግር “ክብርት ፕሬዝዳንታችን እኛ አሰልጣኞች ለረጅም ጊዜ ለፍተናል፣ለረጅ ጊዜ ትልቅ ነገር አድርገናል፤ ልፋታችንን አይመጥንም” ብሏል።
እኔ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የወርቅና የብር ሜዳሊያ እንዲሁም ዲፕሎማ አስመጥቼ፤ ለዚህ ሀገር ተጋድዬ ለእኔ 2 ሚሊየን የስድብ ያህል ስለሆነ እርሶን ካላስከፋሁ ይህንን ሽልማቴን መመለስ እፈልጋለሁ፤ የመጣው ሁሉ አወቀበላለሁ” ብለዋል።