ኢትዮጵያ በመድረኩ ያገኘቻቸውን ሜዳልያዎች ብዛት 62 አድርሳለች
ትናንት ምሽት በተጠናቀቀው የ2024 ኦሎምፒክ አፍሪካውያን አትሌቶች ባልተጠበቁ ውድድሮች አሸንፈዋል።
ቦትስዋና በወንዶች የ200 ሜትር ሩጫ በሌስል ቶቦጎ አማካኝነት በኦሎምፒክ መድረክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ በፓሪስ ማሳካት ችላለች።
አልጀሪያም በአርትስቲክ ጂምናስቲክ ለሀገሪቱ ብሎም ለአፍሪካ ቀዳሚውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ በካይሊያ ኔሞር አማካኝነት አሳክታለች።
የደቡብ ሱዳን የወንዶች የቅርጫት ኳስ ቡድን በፓሪስ ኦሎምፒክ በመክፈቻው ፖርቶ ሪኮን 90 ለ78 በማሸነፍ ያሳየው ብቃትም አፍሪካውያን ከተለመዱት የአትሌቲክስ ውድድሮች ውጪም ብሩህ ተስፋ እንዳላቸው ማመላከቱ ይታወሳል።
ከ54ቱ የአፍሪካ ሀገራት በ33ኛው ኦሎምፒክ የሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻሉት 12ቱ ብቻ ናቸው።
አራት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና አምስት የነሃስ ሜዳልያዎችን ያገኘችው ኬንያ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ደግሞ 17ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
የኦሎምፒክ ተሳትፎዋን በ1956 በሜልቦርን አሀዱ ያለችው ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ ከአፍሪካ አልጀሪያ እና ደቡብ አፍሪካን ተከትላ 4ኛ፤ ከአለም ደግሞ 47ኛ ደረጃን ይዛለች።
ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በኦሎምፒክ መድረክ ያገኘችውን የሜዳልያ ብዛት 62 አድርሳለች።
በ33ኛው ኦሎምፒክ ከአፍሪካ በሜዳልያ ቀዳሚ የሆኑ 10 ሀገራትንና አለማቀፍ ደረጃቸውን ይመልከቱ፦