ስፖርት
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በፓሪስ ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኘች
የአለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤቷ በ2 ስአት ከ22.58 ደቂቃ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች
ፓሪስ ያስተናገደችው 33ኛው ኦሎምፒክ ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል
ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ የሴቶች ማራቶን ውድድር የብር ሜዳልያ አገኘች።
ተጠባቂ የነበረችው አትሌት ትዕግስት አሰፋ በውድድሩ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በበርሊን ማራቶን የርቀቱን የአለም ክብረወሰን የሰበረችው አትሌት ትዕግስት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ስአት ከ22 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ፈጅቶባታል።
በፓሪስ ኦሎምፒክ በ5 ሺህ እና 10 ሜትር ውድድር የነሃስ ሜዳልያን ያገኘችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቃለች።
ውድድሩን ያጠናቀቀችበት 2 ስአት ከ22.55 ደቂቃ የኦሎምፒክ ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል።
ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ደግሞ የነሃስ ሜዳልያ አግኝታለች።
ኢትዮጵያ ደካማ ውጤት ያስመዘገበችበት የፓሪስ ኦሎምፒክ ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።
በወንዶች ማራቶን ካስመዘገበችው የወርቅ ሜዳልያ ውጭ በተጠበቀችባቸው ውድድሮች ውጤት የራቃት ኢትዮጵያ 47ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።