በኢትዮጵያ በጎግል ላይ ሰዎች በብዛት የፈለጉት ቃላቶች የትኞቹ ናው?
በኢትዮጵያ በ2023 በብዛት ጎግል ላይ ከተፈለጉ ቃላቶች ውስጥም ኢትዮጵያ (Ethiopia) የሚለው ቃል ቀዳሚ ነው
ጎግል በዓመቱ በብዛት የተፈለጉ ቃላቶችን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በኢትዮያ በብዛት የተፈለጉትም ተካተዋል
ጎግል በፈረንጆቹ 2023 ሰዎች በድረ ገጹ ላይ በመግባት በብዛት የፈረጉትን (ሰርች) ያደረጉትን ቃላቶች ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያም ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2023 በዓመቱ በብዛት ጎግልላይ የተፈለጉ ቃላቶችን አሉ ያሉው ደግሞ ስታሲስታ የተባለ ድረ ገጽ ነው።
በኢትዮጵያ በብዛት ጎግል ላይ ከተፈለጉ ቃላቶች ውስጥም ኢትዮጵያ (Ethiopia) የሚለው ቃል ቀዳሚ ነው የተባለ ሲሆን፤ ዋት ኢስ (What is) እና ቪድዮ (Video) የሚለው ቃል ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።
ቫሙስ ዩ ትዩብ፣ ሚዩዚክ፣ ፕሪምየር ሊግ፣ ትራንስሌት (ትርጉም) ቴልግራም፣ ጂ ሜይል፣ አርሴናል እና ዳወንሎድ የሚሉ ቃላቶችም በብዛት በኢትዮጵያውያን ጎግል ላይ ተፈለጉ ቃላቶች ናቸው ተብሏል።
በ2023 በኢትዮጵያ በጎግል ላይ በብዛት የተፈለጉ ቃላቶች
1 ኢትዮጵያ (Ethiopia)
2 ዋት ኢስ (What is)
3 ቪድዮ (Video)
4 ቫሞስ (Vamos)
5 ዩ ትዩብ (Youtube)
6 ትራንስሌት (Translate)
7 ጎግል (Google)
8 ኢትዮጵያን (Ethiopian)
9 ቫሞስ ቤት (Vamos bet)
10 ፕሪምየር ሊግ (Premier league)
ከጎግል በተጫሪም በዩትዩብ ላይ በኢትዮጵያውያን በበዝት የተፈለጉ ቃላቶችም ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ ሙዚቃ (Music) የሚለው ቃል ቀዳሚውን ደረጃ ይዟል ይላል የስታቲታ ሪፖርት።
መዝሙር (Mezmur) የሚለው ቃል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ኒው ሚዩዚክ (New music) የሚለው ቃልም ሶሰተኛ ደረጃን ይዟል።