ቻይና፣ ህንድ፣ ኬንያ እና ሲሪላንካ ቀዳሚዎቹ ሻይ አምራች ሀገራት ናቸው
ሻይ ከውሃ በመቀጠል የሰው ልጆች በየእለቱ የሚወስዱት ፈሳሽ ነው።
የአለም የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) በ2022 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ቶን ሻይ የተመረተ ሲሆን፥ ቻይና፣ ህንድ፣ ኬንያ እና ሲሪላንካ ቀዳሚዎቹ አምራቾች ናቸው።
ስታስቲስታ ባወጣው የዳሰሳ ጥናት ግን ሻይ በመጠጣት ቀዳሚዎቹ ቱርካውያን ናቸው፤ በጥናቱ ከተካተቱት ውስጥ 87ቱ ሻይ እንደሚጠጡ ተናግረዋል።
በተወዳጁ ትኩስ መጠጥ የሚንቀሳቀሰው ገንዘብ በ2025 134 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ ተገምቷል።
በፈረንጆቹ ግንቦት 21 በየአመቱ የሻይ ቀን ተብሎ ይከበራል። ዜጎቻቸው በብዛት ሻይ ጠጪ የሆኑባቸው ሀገራትን በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦