ኢትዮጵያ በአንድ ምሽት 4 የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸነፈች
ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6 ወርቅን ጨምሮ በ12 ሜዳልያዎችን አሸንፋለች
ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በ12 ሜዳሊያዎች ከዓለም በ3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች
በኮሎምቢያ ካሊ ላለፉት 6 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከ20 ዓመት በታች የወጣቶች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሌሊቱን ፍጻሜውን አግኝቷል።
ሌሊቱን በተካሄዱ የፍጻ ውድድሮች ላይም የኢትዮጵያ አትሌቶች 4 የወርቅ ሜዳሊያዎችን እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችለዋል።
ሌሊት በተካሄዱ የፍጻሜ ውድድሮችም በ1500 ሜትር ሴቶች ብርቄ ሀየሎም፣ በ800 ሜትር ወንዶች ኤርሚያስ ግርማ፣ በ5000 ሜትር ሴቶች መዲና ኢሳ እንዲሁም ወርቅ በ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ሳሙኤል ዱጉና የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝተዋል።
እንዲሁም በ5000 ሜትር ሴቶች መልክናት ውዱ እና በ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ሳሙኤል ፍሬው የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵ የብር ሜዳሊያ አስገኝተዋል።
በአጠቃላይ ለ6 ቀናት በኮሎምቢያ ካሊ ሲካሄድ በቆየው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ቡድን 6ወርቅ፣ በ5ብር እና 1 የነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች ማሸነፍ ችሏል።
በዚህም ሻምፒዮናውን ኢትዮጵያ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀች ሲሆን፤ በሳምፒዮናው አሜሪካ 1ኛ ደረጃ፣ ኢንዲሁም ጃማይካ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪክ ዘንድሮ ያስመዘገበችው ውጤት ከፍተኛው መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አስታውቋል።