አትሌቷ ለኢትዮጵያ 3ኛ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች
የ2022 ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር በአሜሪካ አስተናጋጅነት ኦሪጎን እየተካሄደ ነው።
ከደቂቃዎች በፊት ፍጻሜውን ባገኘው የሴቶች ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያ በሶስት አትሌቶች ተወክላለች።
አትሌት ጎትይቶም ገ/ስላሴ ውድድሩን በ 2 ሰዓት በ18 ደቂቃ ከ 11 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።
ከዚህ በተጨማሪም በእንግሊዛውቷ አትሌት ተይዞ የነበረውን የውድድሩን ክብረወሰን መስበር ችላች።
በውድድ ኬንያ የብር እስራኤል ደግሞ የነሀስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።
አባብል የሻነ እና አሼቴ በክሬ በውድድሩ ላይ ተወዳድረው የነበረ ሲሆን፤ አትሌት አባብል የሻነህ ሁለት ሰዓት ያህል ከሮጠች በኋላ በህመም ምክንያት ውድድሩን አቋርጣለች።
ትናንት ፍጻሜውን ባገኘው የወንዶች ላይ ለሊሳ ደሲሳ፣ታምራት ቶላ፣ ሞስነት ገረመው እና ሴፋ ቱራ ተሳትፈው ኢትዮጵያ በታምራት ቶላ እና ሞስነት ገረመው የወርቅ እና ብር ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል።
ከትናንት በስቲያ ምሽት በተካሄደው የሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ሩጫ ለተሰንበት ግደይ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቅቅ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ ኢትዮጵያ ስታገስገኝ ኬንያውያን አትሌቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
እንዲሁም ትናንት ምሽት 5 ሰዓት ላይ በተካሄደው የ10 ሺህ ወንዶች ሩጫ ኢትዮጵያ ከሜዳሊያ ውጪ መሆኗ አይዘነጋም።
ቻይና፣ፖላንድ፣ጃፓን እና ፔሩ አንድ የወርቅ ሜዳሊያ ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡በዚህ ውድድር ላይ ከአፍሪካ በብቸኝነት ኢትዮጰያ እና ኬንያ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ የገቡ ሀገራት ናቸው፡፡