የወንዶች ማራቶን ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል
አትሌት ታምራት ርቀቱን በ 2 ሰአት ከ5 ደቂቃ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አጠናቋል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሙስነት ገረመው ውድድሩን በሁለተኝነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።
የዘንድሮው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር በአሜሪካዋ ኦሪጎን በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ባሳለፍነው አርብ የተጀመረው ይህ ውድድር እስከ ፈረንጆቹ 24 ቀን 2022 ድረስ በአሜሪካ ኦሪጎን ከተማ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
በውድድሩ ላይ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ዛሬም በተጠባቂ ውድድሮች ቀጥሎ ሲካሄድ ሀገራችን ተጨማሪ ወርቅ እና ብር አግኝታለች።
ለሊሳ ደሲሳ፣ታምራት ቶላ፣ ሞስነት ገረመው እና ሴፋ ቱራ በዚህ የወንዶች ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩ ሲሆን ከኬንያ አትሌቶች ከፍተኛ ፉክክር ገጥሟቸው ነበር።
ትናንት ምሽት በተካሄደው የሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ሩጫ ለተሰንበት ግደይ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቅቅ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ ኢትዮጵያ ስታገስገኝ ኬንያውያን አትሌቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
እንዲሁም መሽት 5 ሰዓት ላይ ደግሞ የ10 ሺህ ወንዶች ሩጫ ንጋት 11 ሰዓት ላይ ደግሞ የወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉም ተብሏል፡፡
እስካሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ 11 ሀገራት የሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ የገቡ ሲሆን አሜሪካ በሁለት ወርቅ እንዲሁም ቻይና፣ፖላንድ፣ጃፓን እና ፔሩ አንድ የወርቅ ሜዳሊያ ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡
በዚህ ውድድር ላይ ከአፍሪካ በብቸኝነት ኢትዮጰያ እና ኬንያ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ የገቡ ሀገራት ናቸው፡፡