የኢሬቻ በዓል አከባበር በፎቶ
የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው
የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆረ ፊንፊን የኢሬቻ በዓል በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ለ3ኛ ጊዜ ተከብሯል
የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆረ ፊንፊን የኢሬቻ በዓል በዛሬው እለት ለሶስተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ተከብሮ ውሏል።
ከአዲስ አበባ እና ከዙሪያዋ እንዲሁም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ለበዓሉ በባህል አልባሳት ደምቀው በሆራ ፊንፊኔ በመገኘት ኢሬቻውን በአንድነት አክብረዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች ውብና ማራኪ በሆኑ ባህላዊ አልባሳትና እሴቶች አሸብርቀው፣ ባህላዊ ጭፈራዎችን ልዩ ልዩ ዜማዎችን በማዜም በዓሉን አክብረዋል።
ፈረስኞችም የተለያዩ ትርኢቶችን እያሳዩ ሲሆን፤ ከሲዳማ፣ ከወላይታ፣ ከሃላባ እና ከሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተውጣቱ የቤህር በሄረሰቦች ተወካዮች በበዓሉ ላይ ተለያዩ ትርኢቶችን አሳይተዋል።