የኢሬቻ በዓል ተከበረ
የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆረ ፊንፊን የኢሬቻ በዓል በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ለ3ኛ ጊዜ ተከብሯል
የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው
የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆረ ፊንፊን የኢሬቻ በዓል በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ተከብሯል።
የበዓሉ ስነ ስርዓት የተጀመረው በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባ ገዳዎች ምርቃት ነው።
በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆራ ፊንፊኔ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበው ወደ መጡበት ተመልሰዋል።
ከአዲስ አበባ እና ከዙሪያዋ እንዲሁም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ለበዓሉ በባህል አልባሳት ደምቀው በሆራ ፊንፊኔ በመገኘት ኢሬቻውን በአንድነት አክብረዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች ውብና ማራኪ በሆኑ ባህላዊ አልባሳትና እሴቶች አሸብርቀው፣ ባህላዊ ጭፈራዎችን ልዩ ልዩ ዜማዎችን በማዜም በዓሉን አክብረዋል።
ፈረስኞችም የተለያዩ ትርኢቶችን እያሳዩ ሲሆን፤ ከሲዳማ፣ ከወላይታ፣ ከሃላባ እና ከሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተውጣቱ የቤህር በሄረሰቦች ተወካዮች በበዓሉ ላይ ተለያዩ ትርኢቶችን አሳይተዋል።
የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው።
ኢሬቻ የምስጋናና የምልጃ በዓል ሲሆን በዚህ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉን ነገር ለፈጠረው ምድርንና ሰማይን፣ ወንዝንና ባህርን፣ ቀንንና ሌሊትን፣ ብርሀንና ጨለማን፣ ሕይወትና ሞትን፣ ክረምትንና በጋን፣ ዝናብንና ሐሩርን፣ ዕጽዋትን፣ እንስሳትንና ሰውን ለፈጠረ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ለሚችል “ዋቃ” (አምላክ) ምስጋናና ክብር የሚያቀርብበት በዓል ነው።