የኢትዮጵያ ከ20 በታች ብሄራዊ የሴቶች ቡድን ሁሉንም ጨዋታዎች አሸንፈዋል
ኢትዮጵያ የስቶች ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ዋንጫን አሸነፈች፡፡
የሴካፋ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዋንጫ ጨዋታ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ዛሬ ተቻውተዋል፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዙሩ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች ሁሉንም በአሸናፊነት አጠናቋል፡፡
ዛር በተደረገው ጨዋታም ዩጋንዳ አስከ እረፍት ድረስ 2 ለ0 በሆነ ውጤት ብትመራም ኢትዮጵያ ከእረፍት መልስ ረድኤት አስረሳከኝ፣አርያት ኦዶንግ እና ቱሪስት ለማ ባስቆጠሯቸው ሶስት ጎሎች ውድድሩን 3 ለ2 በማጠናቀቅ የዋናጫ ባለቤት ሆናለች፡፡
በውድድሩ ኢትዮጵያ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ በቅደም ተከተሉ መሠረት የብርና የንሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።.
የ2021 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪ ሀገራት ውድድር (ሴካፋ) ዋንጫ በስድስት ሀገራት መካከል በዙር ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ ባደረጋቸው 5 ጨዋታዎች ሁሉንም አሸንፏል፡፡
በውድድሩ 10 ጨዋታዎች ላይ 57 ጎሎች የተቆጠሩ ሲሆን ጅቡቲ እስካሁን በሁሉም ጨዋታዎች ተሸንፋለች፡፡