አትሌት አባበል የሻነህ በሴቶች ማራቶን ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች
ኬንያውያን የኒዮርክ ማራቶንን በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ፡፡
ዛሬ ሌሊት በተካሄደው 50ኛው የኒዮርክ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኬንያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡
በሴቶች የማራቶን ውድድር በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ለአገሯ ያስገኘችው አትሌት ፔሬዝ ጄፕቺርችር ርቀቱን 2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ39 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች፡፡
ሌላኛዋ ኬንያዊ ቪዮላ ቼፕቱ ውድድሩን ሁለተኛ ስታጠናቅቅ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባበል የሻነህ ደግሞ በሶስተኝነት ማጠናቋን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡
አትሌት ዳዊት ስዩም በ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበች
የውድድሩ አሸናፊዎች ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማትን ያገኛሉ፡፡ ፔሬስ ጄፕቺርቺር 100 ሺ ዶላር፣ ቫዮላ 60 ሺ ዶላር እንዲሁም አባብል 40 ሺ ዶላር ያገኛሉ፡፡
በወንዶች ተመሳሳይ ውድድር ደግሞ አትሌት አልበርት ኮሪር ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ08 ደቂቃ ከ22 ማይክሮ ሰከንድ በአንደኝነት አጠናቃል፡፡
ሞሮኳዊው መሀመድ ኤል አራባይ የወንዶች ማራቶንን ሁለተኛ ጣልያናዊው ኢዮብ ፋኑኤል ሶስተኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
ለአሸናፊነት ሲጠበቅ የነበረው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ52 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ 6ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡
አትሌት ቀነኒሳ በውድድሩ ላይ በጥሩ ብቃት ላይ እንደነበረ ተናግሮ ነገርግን ውድድሩን ማሸነፍ አለመቻሉን ከውድድሩ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡