ፖለቲካ
ለሴካፋ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ዛሬ ይጫወታሉ
የዘንድሮው የሴካፋ ዋንጫ በኡጋንዳ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ ይገኛል ውድድሩ ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል
ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ ዛሬ በኡጋንዳ አስተናጋጅነት ለዋንጫ ይጫወታሉ
የዘንድሮው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪ ሀገራት ውድድር (ሴካፋ) ዋንጫ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ ሁሉንም ውድድሮች በማሸነፍ 12 ነጥብ በመያዝ በጎል ተበላልጠው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ ባደረጋቸው 4 ጨዋታዎች ሁሉንም አሸንፏል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይም 12 ነጥብ ካለው ዩጋንዳ አቻው ጋር የዋንጫ ጨዋታ እንደሚያደርግ ከውድድሩ መርሃግብር ተረድተናል፡፡
ከዋናጫው ጨዋታ በፊት ግን ቡሩንዲ ከኤርትራ፣ ጅቡቲ ከታንዛኒያ ሶስተኛ ደረጃኘ ለመያዝ ይጫወታሉ ፡፡ በእስካሁኑ የውድድሩ ዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ 52 ጎሎች የተቆጠሩ ሲሆን ጅቡቲ እስካሁን በሁሉም ጨዋታዎች ተሸንፈዋል፡፡