በፊሊፒንስ የሚገኝ ኮሌጅ ተማሪዎች ፈተና እንዳይኮራረጁ “ጭንቅላታችሁን ሸፍኑ” ማለቱ እያነጋገረ ነው
አብዛኞቹ ተማሪዎች ፈተናውን በአግባቡ መፈተኛቸውንና እየኮረጀ የተያዘ ተማሪ አለመኖሩን ኮሌጁ አስታውቋል
“የፀረ ኩረጃ ኮፍያ” የተባለውን ያደረጉ ተማሪዎችን የሚያሳዩ ፎቶግራች በርካቶችን አስገርሟል
በፊሊፒንስ በኮሌጅ ፈተና ላይ “የፀረ ኩረጃ ኮፍያ” የሚል መጠሪያ በተሰጠው መሸፈኛ ራሳቸውን ከልለው ፈተና ሲፈተኑ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ከሰሞኑ በማበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋሪያ ሆኖ ሰንብቷል።
በፊሊፒንሷ ልጋዝፒ ከተማ የሚገኝ አንድ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኝ ኮሌጅ ተመሪዎች ወደጎናቸው አጮልቀዉ በመመልከት ፈተና እንዳይሰርቁ በማሰብ ጭንቅላታቸውን የሚሸፍን ነገር እንዲለብሱ ታዘዋል።
ይህንን ተከትሎም ተማሪዎች ካርቶኖችን፣ የአንቅላል መደርደሪያዎችን፣ የሞተር ሳይክል ሄልሜት እንዲሁም ከሌሎች የወዳደቁ ነገሮች በራሳቸው ፈጠራ የሰሯቸውን መሸፈኛዎች ለብሰው በፈተናው ላይ መገኘታውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በባይኮል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ ማንዳን፤ ተማሪዎች እንዳይኮራረጁ የተተገበረው አሰራር ውጤናማ እንደበረ አስታውቀዋል።
በፈተና ወቅት ፊት መሸፈን እንዲተገበር ያነሳሳቸው ከዓመታት በፊት በታይላንድ ውስጥ ተተግብሮ ያዩት አንደሆነም ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ ተናግረዋል።
በፈረንጆጁ 2013 ላይ የባንኮክ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፈተና ላይ በሚቀመጡበት ወቅት በግራና በቀኝ በኩል ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ በወረቀት እንዲሸፍኑ በማድረግ ፈተና እንዲፈተኑ ተደርጎ ነበር።
ከዚህ በመነሳት “የፀረ ኩረጃ ኮፍያ” በባይኮል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ መተግበሩንም ፐሮፌሰሯ አስታውቀዋል።
ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ፤ ጥብቅ የፈተና ቁጥጥር ተማሪዎች ለማጥናት አነሳስቷል ያሉ ሲሆን፤ ይህም የተሸለ አፈጻጸም ማስገኘቱንም ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት በርካቶች ፈተናቸውን በአግባቡ እና በተሰጣቸው ጊዜ ማጠናቀቃቸውን የገለጹት ፕሮፌሰሯ፤ ፈተና ሲሰርቅ የተያዘ ተማሪ እንደሌለም አስታውቀዋል።