በየአራት ዓመቱ የሚከለሰው የክፍያ ተመኑ እስከ 300 ኪሎ ዋት ድረስ ለሚጠቀሙ እስከ 75 በመቶ ድጎማ ይደራገል ተብሏል
አዲሱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክፍያ ተመን ሲፈተሸ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዛሬ መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበር አዲ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ተመን ይፋ አድርጓል፡፡
አዲሱ የክፍያ ተመን ማሻሻያ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየሩብ ዓመቱ ተከፋፍሎ ለ4 ተከታታይ ዓመታት ማለትም እስከ እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ ተገበራል ተብሏል፡፡
በዚህም ከ0 እስከ 300 ሜዋት/ሰ የሚጠቀሙ ደንበኞች የድጎማው ተጠቃሚ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን ከ50 ኪዋት/ሰ በታች ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 75 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፡፡
ከ50 ኪዋት/ሰ እስከ 100 ኪዋት/ሰ ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 40 በመቶ የሚሆነውን እንደሚደጎሙ ተቋሙ አስታውቋል፡፡
እንዲሁም ከ200 ኪዋት/ሰ እስከ 300 ኪዋት/ሰ ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 4 በመቶ ሲደጎሙ ከ400 ኪዋት/ሰ እስከ 500 ኪዋት/ሰ የሚጠቀሙ ደንበኞች ግን የተጠቀሙትን ሙሉ ለሙሉ እንደሚከፍሉ ተገልጿል፡፡
አዲሱ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ተመን የመኖሪያ ቤት፣ የንግድ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዲስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚዎችን የሚመለከት ሲሆን የአገልሎት ክፍያ፣ የሃይል ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ እና የከፍተኛ ሃይል ጭነትን ይጨምራል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአራት ዓመት በኋላ አዲስ የፍጆታ ክፍያ ተመን እንደሚያወጣም አስታውቋል፡፡